ፎረፎር ለማጥፋት የሚረዱ 7 የቤት ውስጥ መፍትሄዎች

ፎረፎር ወይንም ሴቦሪክ ደርማቲቲስ ተብሎ የሚታወቀው ብዙ ሰው ላይ የሚታይ የጭንቅላት ቆዳ በሽታ ነው። በደረቅ ወይም በተቆጣ ቅባታማ ቆዳ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ጭንቅላት ላይ የሚያድጉ ባክቴርያ እና ፈንገሶችም የበሽታው መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በሽታው የጭንቅላታችን ቆዳ እንዲደርቅ እና እንዲያሳክከን ያደርጋል።

የጸጉርን ጤና በመጠበቅ የበሽታውን ስሜቶች መቆጣጠር ይቻላል። ወይም እንዳማራጭ ቤት ውስጥ በምናዘጋጃቸው መፍትሄዎች በሽታውን መቆጣጠር እንችላለን። ፎረፎርን ለማከም ቤት ውስጥ የምናዘጋጃቸው መፍትሄዎች በሽታውን ለማከም ግዜ የሚፈጁ ቢሆኑም ለበሽታው ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጡ ናቸው።

7ባቱ ዘዴዎች እነሆ

1) የኮኮናት ዘይት

የኮኮናት ዘይት ውስጡ ባለው የጸረ ፈንግስ ንጥረ ነገር ፎረፎርን ለማከም ጥሩ መፍትሄ ነው። የጭንቅላታችንንም ቆዳ ልስላሴ በመስጠት የሚያሳክከንን ስሜት ይረዳናል።

መጀመርያ የኮኮናት ዘይቱን ከሱ በመጠን ግማሽ ከሚያንስ የሎሚ ጭማቂ ጋር ማቀላቀል። ከዛ ጭንቅላታችን ላይ ለተወሰን ደቂቃ ማሸት። ከ20 ደቂቃ በኋላ ጸጉራችንን መታጠብ። ይህንን መፍትሄ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ግዜ መደጋገም ያስፈልጋል።

2) አፕል ሳይደር አቸቶ

/

የራስ ቅላችንን በአፕል ሳይደር አቸቶ ማከም ለፎረፎር ፍቱን መፍትሄ ይሆናል። ራስ ቅላችን ላይ ያለውን የፒኤች መጠን ወደ ተፈጥሮአዊ መጠኑ በመመለስ ጸጉራችን ላይ የእርሾ እድገትን ይገታል። አቸቶው የተደፈኑ የጸጉር ክፍተቶችንም በመክፈት የጸጉራችንንም ጤና ይጠብቃል።

ሁለት የሻይ ማንኪያ አቸቶ ከሁለት ሻይ ማንኪያ ውሃ ጋር በማቀላቀል ጸጉራችንን ማሸት ይኖርብናል። ለተወሰነ ደቂቃ አቆይተነው ጸጉራችንን መታጠብ እንችላለን። መፍትሄውን በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ግዜ መደጋገም ይኖርብናል።

ጨርሰን ጸጉራችንን ከታጠብን ብኋላ ብቻ ነው ሻምፑ መጠቀም የምንችለው።

3) የመጋገርያ እርሾ

እርሾ በቅላችን ላይ የሞቱ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል። ጭንቅላታችን ላይ ያለውን ትርፍ ዘይት ይመጣል። የቅላችንን ፒኤች መጠን በማመጣጠን የጸጉር ፈንገስ ይቀንሳል።

መጀመርያ ጸጉራችንን አርጥበን የአንድ መዳፍ መጠን ያሆነ እርሾ ጸጉር ላይ አድርጎ ማሸት። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ጸጉራችንን በሙቅ ውሃ መታጠብ። ለተወሰኑ ሳምንታት በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ግዜ ማድረግ በቂ ነው።

ጨርሰን ጸጉራችንን ከታጠብን ብኋላ ብቻ ነው ሻምፑ መጠቀም የምንችለው።

4) ነጭ አቸቶ

ነጭ አቸቶ ለፎረፎር ዋነኛ መፍትሄ ነው። ውስጡ የያዘ አሴቲክ አሲድ የጸጉር ፈንገስ ያጠፋል። ማሳከክም ይቀንሳል።

አንድ ግማሽ ስኒ አቸቶ ከሁለት ሲኒ ውሃ ጋር በማቀላቀል ጸጉርን በደንብ ማሸት። እንደ አማራጭ ቅላችንን በሁለት ስኒ አቸቶ፣ አንድ ሲኒ ወይራ ዘይት እና ሶስት ስኒ ውሃ አቀላቅሎ ለ10 ደቂቃ ማሸት።

አንደኛውን አማራጭ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ማድረግ በቂ ነው።

5) የወይራ ዘይት

የራስ ቅል መድረቅን ልስላሴ ይዘት ባለው በወይራ ዘይት መታከም ይቻላል።

 • የወይራ ዘይቱ ትንሽ ሞቅ እስኪል እሳት ላይ መጣድ
 • ጭንቅላታችን ላይ ካሹ በኋላ ጸጉራችንን በፎጣ መጠቅለል
 • ለ45 ደቂቃ እንደተጠቀለለ መተው። ከዛ ጸጉራችንን በደንብ መታጠብ
 • መፍትሄውን በሳምንት ለተወሰኑ ግዚያቶች መደጋገም አስፈላጊ ነው።

6) የሎሚ ጭማቂ

ulleo / Pixabay

የሎሚ ጭማቂ ጸረ ፈንገስ የሆነ አሲዳማዊ ይዘት አለው። የማሳከክ ስሜት ለማጥፋትም ይረዳናል።

 • ግማሽ ሎሚ ከሩብ ስኒ እርሾ ጋር ቀላቅለን ማቀላቀል።
 • ውህዱን ጸጉር እና ራስ ቅላችን ላይ ማሸት።
 • ለ20 ደቂቃ ጭንቅላታችን ላይ ከተውነው በኋላ ማጠብ
 • በሳምንት ለተወስነ ግዜ ማድረግ ያስፈልጋል።

7) አስፕሪን

padrinan / Pixabay

አስፕሪን በውስጡ ሳሊሳይክሊክ አሲድ የሚባል ፎረፎርን መቆጣጠር የሚችል ንጥረ ነገር ይዟል።

 • ሁለት የአስፕሪን ክኒኖችን ማድቀቅ
 • ከትንሽ ሻምፑ ቅባት ጋር ማቀላቀል።
 • ጸጉራችንን በውህዱ ካሸን ብኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች መተው።
 • ጸጉራችንን ደጋግመን ማጠብ

ግር ላይ የተወሰኑ መረጃዎች እነሆ:-

ፎረፎር ብዙ ጊዜ የሚከሰትና የራስ ቆዳ እየተቀረፈ እንዲፈረፈር፣ እነዲላላጥና እንዲራገፍ የሚያደርግ የራስ ቆዳ ችግር ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ፎረፎር ከአንድ ሰዉ ወደሌላ ሰዉ የማይተላለፍና ከፍ ያለ ችግር የማያስከትል የቆዳ ችግር ቢሆንም ሀፍረትን ሊያስከትል እና ለህክምና አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለፎረፎር ጥሩ ነገሩ በቀላሉ መቆጣጠር መቻሉ ነዉ፡፡ ቀላል የፎረፎር አይነት በተከታታይነት በሻምፖ ከማፅዳት በላይ ብዙ የተለየ ነገር ማድረግ አያስፈልገዉም፡፡ ከፍ ያለ የፎረፎር አይነት ከሆነ ግን ፎረፎርን ለማከም የሚረዱ የሻምፖ አይነቶችን በመጠቀም ችግሩ እንዲቃለል ማድረግ ይችላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች
ለብዙዉዎቹ ታዳጊዎችና አዋቂዎች ፎረፎርን እንዳዩት መለየት በጣም ቀላል ሲሆን ምልክቶቹ ነጭ የሆነ፣ ነጠብጣብ መሳይ ወዝነት ያለዉ በፀጉርና በትከሻ ላይ የሚራገፍ የሞቱ የቆዳ ሴሎች፣ ማሳከክና የራስ ቆዳ እንደ ቅርፊት መቀረፍ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ ይህ ችግር የቆዳን መድረቅ ሊያባብሱ የሚችሉ ሞቃታማ የአየር ሁኔታዎች ወቅት የሚባባስ ሲሆን በቀዝቃዛማ ወቅቶች ችግሩ ይቀንሳል፡፡
ህፃናት ላይ ክረድል ካፕ( cradle cap ) የሚባለዉ የፎረፎር አይነት ሚታይ ሲሆን ምልክቶቹ ከህፃናቱ ጭንቅላት ላይ እየተቀረፈ የሚነሳ ነገር ይታያል፡፡ ይህ ሁኔታ አብዛኛዉ ጊዜ በጨቅላ ህፃናት ላይ የሚታይ ቢሆንም በየትኛዉም የህፃንነት እድሜ ክልል ሊታይ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ወላጆችን የሚያሳስብ ጉዳይ ቢሆንም ክረድል ካፕ በህፃናቱ ላይ የሚያመጣዉ ጉዳት የሌለ ከመሆኑም በላይ የልጁ እድሜ 3 አመት እየሆነዉ ሲሄድ ችግሩ በራሱ ጊዜ እየጠፋ ይመጣል፡፡

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
ብዙዎቹ የፎረፎር ችግሮች የህክምና ባለሙያ እገዛ/ምክር አያስፈልጋቸዉም፡፡ ነገር ግን ለሳምንታት ያህል ያለሀኪም ትእዛዝ ሊገዙ የሚችሉትን የፎረፎር ሻምፖዎች እየተጠቀሙ ቆይተሁ አሁንም ፀጉርዎ የሚያሳክኮት ከሆነ፣ ወይም የራስ ቆዳዎ ከቀላ ወይም ካበጠ የህክምና ባለሙያዎን ወይም የቆዳ ህክምና ባለሙያዎችን ያማክሩ፡፡ ምናልባት ከፎረፎር ጋር ተመሳሳይነት ያላቸዉ ሌላ ነገር ወይም ሴቦሪክ ደርማታይትስ የሚባለዉ ችግር ሊሆን ስለሚችል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ የህክምና ባለሙያዎ ያለተጨማሪ ምርመራ ፀጉርዎንና የራስ ቆዳዎን በማየት ችግሩን ሊለይ ይችላል፡፡
የፎረፎር ምክንያቶች፡- ፎረፎር የተለያዩ መንስኤዎች ያሉት ሲሆን የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡
• የቆዳ ድርቀት፡- የቆዳ ድርቀት ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት አይነተኛ ምክንያት ነዉ፡፡ ከደረቀ ቆዳዎ የሚራገፉ ነገሮች በጣም መጠኑ ትንንሽ የሆኑ ቡናኝና ወዝነት የሌለዉ ሲሆን ምናልባትም ከራስ ቆዳዎ ዉጪ በሌላ የሰዉነትዎ ክፍልዎ ላይ ድርቀት ሊታይ ይችላል፡፡
• ሴቦሪክ ደርማታይትስ(የተቆጣ፣ወዛማ ቆዳ)፡- ይህ ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ አንዱ ሲሆን ዋና መለያዉ ቀይ፣ ወዛማ ቆዳ ሆኖ የተፈረፈረ ነጭ ወይም ቢጫማ ቅርፊት መሳይ ያለዉ የቁዳ መልክ ነዉ፡፡ ሴቦሪክ ደርማታይትስ ቅባትነት ያለዉ ፈሳሽ የሚመነጩ ዕጢዎች( oil glands) በብዛት በሚገኙበት የራስ ቆዳን ጨምሮ እንደ ቅንድብ፣ የአፍንጫ ግራና ቀኝ፣ የጆሮ ግንድ፣ በጡት መካከል በደረት ላይ ባለዉ አጥንት ላይ፣ ብሽሽትና አንዳንዴ ብብት ስር በብዛት ይከሰታል፡፡
• በብዛት የማይታጠቡ ከሆነ፡- ፀጉርዎን ተከታታይነት ባለዉ መልኩ የማይታጠቡ ከሆነ የራስዎ ቆዳ የሞቱ ሴሎችና ወዝ በላይ በላዩ ስለሚደራረብ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡
• ሌላ የቆዳ በሽታ ሲኖር፡- ኤክዜማ ወይም ሶሪያሲስ የሚባሉትን የቆዳ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ፎረፎር ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡
• ፈንገስ(ማላሴዚያ)፡- ማላሴዚያ የሚባለዉ የፈንገስ አይነት በአብዛኛዉ ሰዎች የጭንቅላት ቆዳ ላይ የሚኖር ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ የጭንቅላት ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ አለዉ፡፡ ይህ ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ ብዙ የቆዳ ሴሎች በጭንቅላት ቆዳ ላይ እንዲያድጉ ስለሚደርግ እነዚህ በገፍ ያደጉት ሴሎች ሲሞቱ ነጭ፣ ወዛማ ነገር ሆነዉ በፀጉርና ትከሻዎ ላይ ይራገፋሉ፡፡
• ለፀጉር ዉበት መጠበቂያነት የሚጠቀሙት ነገሮች በጭንቅላት ቆዳዎ ላይ አለርጂ ካመጣብዎ (ኮንታክት ደርማታይትስ/contact dermatitis)፡- አንዳንድ ለራስ ለፀጉር መዋቢያነት የሚጠቀሙባቸዉ ነገሮች ወይም ቀለሞች አንዳንድ በዉስጣቸዉ ያሉ የተሰሩባቸዉ/የተቀመሙባቸዉ ነገሮች (ለምሳሌ ፓራፌኒይልኢንዳሚን) በራስ ቆዳዎ ላይ የመቅላት፣ የማሳከክና መቀረፍ ባህሪይ እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡ በጣም በተደጋጋሚ መታጠብ ወይም የፀጉር ዉበት መጠበቂያ ዉጤቶችንም አብዝቶ መጠቀም የጭንቅላት ቆዳዎን በመቆጥቆጥ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡

የፎረፎርን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች
ሁሉም ሰዉ እኩል በሚባል ደረጃ ፎረፎር የመያዝ እድል ቢኖራቸዉም የተወሰኑ ነገሮች/መንስኤዎች ተጋላጭነትዎን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ እነርሱም
• እድሜ፡- ፎረፎር ብዙዉን ጊዜ በወጣትነት እድሜ የሚከሰት ሲሆን እስከ መካከለኛዉ የእድሜ ክልል ሊዘልቅ ይችላል፡፡ይህ ማለት ፎረፎር በጎልማሳነትና በእርጅና ወቅት አይከሰትም ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ፎረፎር እስከ እድሜ ልካቸዉ ላይተዋቸዉ/ላይጠፋላቸዉ ይችላል፡፡
• ወንድ መሆን፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ ፎረፎር ስለሚበዛ አንዳንድ ተመራማሪዎች ይህ ክስተት ከወንዶች ሆርሞን ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡ ሌላዉ በወንዶች ላይ ለፎረፎር መከሰት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በጭንቅላት ቆዳቸዉ ላይ ብዙ የስብ እጥዎች አሉዋቸዉ፡፡
• ወዛማ ፀጉርና የራስ ቆዳ፡- ማላሴዚያ የሚባለዉ የፈንገስ አይነት በጭንቅላት ቆዳ ላይ ያለዉን ስብ/ዘይት መሳይ ነገር የሚመገብ ሲሆን በጣም የበዛ ወዛማ ቆዳና ፀጉር ለፎረፎር መጋለጥ/መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
• ያልተመጣጠነ ምግብ (Poor diet):- የሚመገቡዋቸዉ ምግቦች እንደ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ና የተወሰኑ የስብ ዘሮችን የማይመገቡ ከሆነ ለፎረፎር ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
የተወሰኑ ህመሞች ፡- ምክንያቱ በዉል/በትክክል ባይታወቅም የነርቭ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች(ምሳሌ ፓርኪንሰን)፣ኤች አይ ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ፣ ከተወሰነ አስጨናቂ ህመሞች እያገገሙ ያሉ( ስትሮክ፣የልብ ችግር) እና የሰዉነት በሽታ የመከላከል አቅም የቀነሰባቸዉ ሰዎች ለፎረፎርና መሰል የቆዳ ችግሮች የተጋለጡ ናቸዉ፡፡

የፎረፎር ህክምና
ፎረፎርን በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ትዕግስትና ሳይታክቱ ክትትል ይፈልጋል፡፡ የፀጉርን ንፅህና መጠበቅ የቆዳዉንና የፀጉሩን ወዛማነትና የሞቱትን ሴሎች ስለሚቀንስ መጠነኛ የፎረፎር ችግሮችን እንዲቀንሱ ያደርጋል፡፡
የተለያዩ የፎረፎር ሻምፖዎች ያሉ ሲሆን እንደሚይዙት መድሃኒት እንደሚከተሉት ይከፈላሉ፡፡
• ዚንክ ፓይሪቲዮን ሻምፖ( Zinc pyrithione shampoos)፡- ይህ ፀረ ባቴቴሪያና ፀረ ፈንገስ መድሃኒት የያዘ ሲሆን ፎረፎርን ለመቀነስ ያገለግላል::
• ታር ቤዝድ ሻምፖስ- Tar-based shampoos (ለምሳሌ ንዩትሮጅን ቲ ጄል)፡- ነዳጅ ሲጣራ ተረፈ ምርት የሆነዉ ኮል ታር የቆዳ ሴሎች የመሞትና የመራገፍ ሂደትን በመቀነስ ለፎረፎር፣ ለሰቦሮይክ ደርማታይትስና ሶሪያሲስ ለመሳሰሉ የቆዳ ችግሮች ህክምና ያገልግላል
• ሳሊሲሊክ አሲድ የያዙ ሻምፖዎች፡- ይህ የቆዳን መቀረፍ ያስወግዳል፤ ነገር ግን ቆዳዎ እንዲደርቅ ስለሚያደርግ ለበለጠ የቆዳ መፈግፈግ ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡ ስለሆነም ድርቀቱን ለመከላከል ሻምፖዉን ከተጠቀሙ በኃላ ኮንዲሽነር መጠቀም ችግሩን ያቃልለዋል፡፡
• ሴሊንየም ሰልፋይድ ሻምፖዎች(ምሳሌ ሴልሰን ብሉ)፡- ሴሊሰን ብሉ የቆዳ ሴሎችን የመሞት ሂደትንና ማለሴዚያ ፈንገስን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
• ኬቶኮናዞል ሻምፖ -Ketoconazole shampoos (ምሳሌ-ኒዞራል)፡- ኬቶኮናዞል ሻምፖ ኬቶኮናዞል የሚባለዉን ፀረ ፈንገስ መድሃኒት የያዘ ሲሆን ሌሎች የሻምፖ አይነቶች ሳያሽሉ ሲቀሩ የሚሰጥ ነዉ፡፡

ከእነዚህ ሻምፖዎች አንዱን ፎረፎሩ እስኪሻልዎ አንድ ቀን እያለፉ መጠቀም፤ ከዚያን በሳምንት ሶስት ቀን ብቻ ማድረግ፡፡ አንዱ ሻንፖ ለዉጥ እያሳየ ቆይቶ የመስራት አቅሙ ከቀነሰብዎ ሌላ የሻምፖ አይነት በመግዛት እያፈራረቁ መጠቀም፡፡ ሻምፖዉን ሲጠቀሙ በደንብ ከራስ ቅል ቆዳዎ ጋር ማሸት፣ ከዚያን ለ5 ደቂቃዎች መጠበቅ (ይህ በሻምፖ ዉስጥ ያለዉ መድሃኒት እንዲሰራ እድል ይሰጠዋል)፡፡ ሻምፖዎችን ለተወሰኑ ሳምንታት ተጠቅመዉ ምንም አይነት ለዉጥ ከሌለዉ የቆዳ ህክምና ባለሙያ ማማከር ይመከራል፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this:
SPONSORSHIP BENEFITS