ፖርቹጋል በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የ5ጂ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ከተማ ይፋ አደረገች

በፖርቹጋል ለመጀመሪያ ጊዜ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥባትን ከተማ ይፋ አድርጋለች።ኤን ኦ ኤስ የተሰኘው የፖርቱጋል ቴሌኮም ኩባንያ እንዳስታወቀው፥ በበሀገሪቱ ሰሜን ፖርቶ ግዛት የምትገኘው ማቶሲኖስ ከተማ የ5 ጂ ኢንተርኔት አግልግሎት መስጠት መጀመሯን አስታውቋል።ይህም ከተማዋን በፖርቹጋል የመጀመሪያዋ የ5 ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥባት ከተማ ያደርጋታል።የ5 ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ስርዓት ዝርጋታው ከቻይናው ቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ጋር በቅንጅት የተሰራ መሆኑ ታውቋል።አገልግሎቱ በከተማዋ ይፋ መደረጉን ተከትሎም በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማት እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ የሙከራ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተመላክቷል።ኤን ኦ ኤስ 5ጂ የተሰኘው ይህ የኢንተርኔት አገልግሎት በከተማዋ መጀመር በአካባቢው ያለውን የበይነ መረብ አገልግሎት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሻሽለው ታምኖበታል።ከዚህ ባለፈም የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ከተሞችን ከቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ጋር ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑ ተገልጿል።ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

Leave a Reply

%d bloggers like this:
SPONSORSHIP BENEFITS